Song Lyrics

የምትረዳ የምታስደግፍ

Netsanet Assefa
Alegn Bizu Misgana
የማትለወጥ ሁሌ እውነተኛ አንተ ነህ ኢየሱስ ለኔ ጋደኛ ወዳጅ እንዳንት የለም ክብር ለዘለዓለም ወዳጅ እንዳንት የለም ክብር ለዘለዓለም የልቤን ሃሳብ የማጫውትህ የእኔ ማረፍያ ወዳጄ እንተ ነህ ይኸው በዘመኔ ይህንን አየሁ እንዳተ የሚሆን አንዳችም አጣሁ ይኸው በዘመኔ ይህንን አየሁ እንዳተ የሚሆን አንዳችም አጣሁ ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ ለእኔ ጌታ ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ አዳኝነትህ ተመችቶኛል በቀን በሌሊት ልቤ ያስብሃል አትሰለችም ሁሌ ባወራህ ልቤም ስለዚህ አንተን ፈለገህ አትሰለችም ሁሌ ባወራህ ልቤም ስለዚህ አንተን ፈለገህ ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ ለኔ ጌታ ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ ከሃዘኔ ስታጽናናኝ መከራዬንም ስታስረሳኝ የልቤ ደስታ አንተ ስትሆን ይህን አይቼ ወደድኩህ አንተን የልቤ ደስታ አንተ ስትሆን ይህን አይቼ ወደድኩህ አንተን ፡ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ ለኔ ጌታ ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ ልቤ እንደ ድንግል ይወድሃል አንተን ሲያስብህ ደስ ይለዋል የእኔ ሙሽራ ኢየሱስ ጌታዬ ፊትህን ሳይ ነው ፍጹ ደስታዬ የእኔ ሙሽራ ኢየሱስ ጌታዬ ፊትህን ሳይ ነው ፍፁም ደስታዬ ማን ይተካል ታዲያ በአንተ ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ ለኔ ጌታ ለማንም አልሰጥም የአንተን ቦታ ኢየሱስ ብቻ ነህ የእኔ ጌታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection