መንገድ አለው ጌታ እርሱ መንገድ አለው መንገድ አለው ጌታዬ እርሱ መንገድ አለው መንገድ አለው ጌታ እርሱ መንገድ አለው መንገድ አለው ጌታዬ እርሱ መንገድ አለው ባሕርን የሚከፍል ንፋስን ያመጣል ውሃውን አስወግዶ መንገድ ያደርገዋል ኃይለኛውንም ወንዝ እርሱ ያቆመዋል ደርቅ መንግድ አድርጐ ማሻገር ይችላል በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም ኤልሻዳይ ነው የሚሳነው የለም ተራራውን አዞ ይደለድለዋል ሸለቆውን ከፍ አድርጐ መንገድ ያደርገዋል የእግዚአብሔር መንገድ በቀን ብቻ አይደለም ሌሊቱም በእርሱ ዘንድ ጨለማ አይሆንም በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም ኤልሻዳይ ነው የሚሳነው የለም ደመናም ባይታይ ነፍሱም ባይነፍስም ለመጽናናት የሚሆን ምልክት ባይኖርም መንገድ አለው ጌታ ውሃውን ያመጣል የሌለውን ጠርቶ ማኖር ያውቅበታል በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም ኤልሻዳይ ነው የሚሳነው የለም