እስቲ እንደ አምላክንትህ እኔ ልፍራህ እስቲ እንደ አባትህ ላክብርህ እስቲ እንደ ንጉሥነትህ ልገዛልህ እስቲ እንደ አዳኝነትህ ልውደድህ እንደ አምልካንትህ እኔ ልፍራህ ላምልክህ እርሱን ብቻ ይሁን የምጠራው ቅዱስ ስምህ ቀኑን ሁሉ አንተን እየፈራሁኝ ልኑር እንተ ብቻ ለኔ አምላኬ እግዚአብሔር እንደ አባትነህ ላክብርህ ልቅረብህ ደስ ያሚያሰኘኝም ይሁንልኝ ፈቃድህ አባ አባ ብዬ እንደ አባቴ ልጠይቅህ የከበረ ይሁን በእኔምዘንድ ስጦታህ እንደ ንጉሥነትህ ልታዛዝህ ልገዛልህ የሚያስተዳድረኝ ቃልህ ይሁን ትህዛዝህ ሥልጣንህም ይግዛኝ ያንበርክከኝ ስረአት ያሲዘኝ በፊትህ ልዋረድ ክብርህም ያስጐንብስኝ እንደ አዳኝነትህ ልወደድህ ልቀኝልህ ክብሬ ትዋረድልህ ያለኝን ሁሉ ለአንተ ልስጥህ ነፍሴም ተጠቅልላ እንተን አንተን ብቻ ትበል በእንተ ደስ እያላት ትጠንልህ ቸል ሳትል