Song Lyrics

እሰይ አባት አለን በሰማይ

Netsanet Assefa
Layih Nafkalew
እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ አባት አለን በሰማይ ወፎች ሚመግባቸው አበቦችን ያሳመራቸው ከእነርሱ አስበልጦናል አባታችን ያስብልናል ጠላቶች ሳለን የወደደን በውድ ልጁ የታረቀን ስንለምነው ይሰማናል መንፈሱን ያፈስልናል እኛ ክፉዎች ስንሆን ልጆቻንን ከወደድን እርሱ የሰማይ አባታችን ደግ ነው የሚያስብልን እጅግ የሚምር የሚራራ አባት አለ ከእኛ ጋራ እርሱ ነው የእኛ አባታችን ሚያስብ ሚጠነቀቅልን እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ አባት አለን በሰማይ አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን በሰማይ አባት አለን አባ አባ እንድንለው መንፈሱን በእኛ አፈሰሰው ልጆቹ አድርጐናል አባት አለን ያስብልናል ፍጻሜና ተስፋ ሰጭያችን እርሱ የሰላም አምላካችን እግዚአብሔር ይወዳናል ክማንም ይልቅ ቀርቦናል እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ አባት አለን በሰማይ አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን በሰማይ አባት አለን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection