አምላኬ ከፍ ከፍ አድርግሃለሁ ስምህን ለዘላላም እባርካለሁ እጅግ የተመሰግንህ እግዚአብሔር ታላቅ ነህ ለታላቅነትህ ፍጻሜ የሌለው ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ርህሩህና መሐሪ ነው ከቁጣ የራቀ ምህረቱ ብዙ ነው ለሚታገሱት እርሱ እግዚአብሔር ቸር ነው ምህረቱ ያምላካችን በስራው ሁሉ ላይ ነው በቃሎችህ አቤቱ አንተ ታማኝ ነህ በስራህም በመንግድህ ሁሉ ጽድቅ ነህ ተስፋ ለሚያደርጉህ ሁሉ አንተ እጅህን ትከፍታለህ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት እግዚአብሔር ለልጅ ልጅ ነው የአንተ ግዛት አቤቱ ስራህ ሁሉ አንተን ያመስግኑሃል ቅዱሳንህም ሁሉ አንተኑ ይባርኩሃል