ነፍሴ የአምላክሽን ክብር እይ ታላቅነቱ ይግባሽ ጌታ መሆኑን ተረጂ ወደ እርሱ ይሁን ልብሽ ቸል አትበይ አትርሺ በዙፋኑ የተቀመጠውን እንደሚገባሽ አክብሪው ማራኪሽ እርሱ ይሁን እኔም ልወቅህ ዛሬ ልወቅህ እንደሚገባኝ በፊትህ ልስገድልህ ክብርህን ጌታ አሳየኝ ክብርህን አይቶ እንደነበረ የሚቀር ማን ነው ብርሃንህን አይቶ የማይሰግድልህስ ማን ነው ነፍሴ እርሱን ማየት ብትችይ ውበቱ ቢታይሽ ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑ ከልብስ ቢረዳሽ ሰላምሽ ይበዛል ታርፊያልሽ ይቀራል ሁከትሽ አምላክ እንደ አምላክነቱ ቢረዳሽ ነፍሴ አምላክሽ ጠርቶሻል የልጁን ክብር እንድታይ በምድር ኑሮ በሚፈርስ በድንክዋን ተይ አትታለይ አምላክ ይረዳሻል መሻትሽ እሱን ብቻ ይሁን ፈልጊው ተጠሚው ተራቢው ጌታሽን ነፍሴ የእምነትን ብልጭታ አንጸባርቆልሻል አምላክ እንድታውቂው እንድትቀርቢው ይሻል አንድ ልጁን ልኮ እንዲሁ በፍቅሩ መርጦሻል ነፍሴ እባክሽ ይግባሽ አክብሪው እርሱ ይበልጥብሻል እዚህ ያደረሰሽ በስጋው መቼ ይለይሻል ሃጢያተኛ ሳለሽ ሞቶልሽ በደሙ አጽድቆሻል ከመልእክት በላይ አክብሮሽ በቀኙ አስቀምጦሻል ነፍሴ እባክሽ ይግባሽ እርሱ አክብሮሻል