Song Lyrics

ደስ ይለኛል በጌታዬ

Netsanet Assefa
Eyesus Fikir
ደስ ይለኛል በጌታዬ ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (2x) እወጣለሁ እገባለሁ እሰማራለሁ የኢየሱስን ሰላም በሕይወቴ አያለሁ በተከበበች ከተማ ምህረቱ ከቦኛል በጌታ ደስ ይለኛል ሰላም ሆኖልኛል አዝ፦ ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ይለኛል በጌታዬ ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (2x) ማህበሉ ቢነሳም እንኳን ወጀቡም ቢበዛ ነፍሴ እረፍት አላት በኢየሱስ ተይዛ በለስ ፍሬ ባታፈራ የወይራ ስራም ቢጐል እኔ ግን በአምላኬ በጌታ ደስ ይለኛል አዝ፦ ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ይለኛል በጌታዬ ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (2x) የልቤ ጥያቄ ሞልቶ ሁሉ ቢሆንልኝ ለእኔስ እንደ ኢየሱስ አንድም አይሆንልኝ የተሰወረውን ነገር የውስጥን ይረዳል በእርሱ ደስ ይለኛል ከሁሉም ይበልጣል አዝ፦ ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ይለኛል በጌታዬ ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (2x) ከታሰርኩበትም ፈቶ ነጻ አድርጐኛል ውዴ በእኔ ላይ ከብሯል ከፍ ብላል ኃጢአቴን አስወግዶልኝ ፅድቄ እርሱ ሆናል በፊቱ ዘላለሁ በጌታ ደስ ይለኛል አዝ፦ ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ይለኛል በጌታዬ ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (2x) ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው ነፍሴን መልሷታል በፅድቅም መንገድ ወደ እውነት መርቷታል በጌታዬ በኢየሱስ በእርሱ እመካለሁ በእርሱ ደስ ይለኛል ለእርሱ እገዛላሁ አዝ፦ ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ይለኛል በጌታዬ ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection