ለናዝሬት ኢየሱስ እንደበግ ለታረደው በደሙ ለእግዚአብሔር ሰዎችን ለዋጀው ለአምላክ መንግሥትና ካህናት ላደረገው በረከትና ክብር ምሥጋና ይድረሰው ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ያለና የነበር የሚመጣው ሁሉን የሚገዛው ኢየሱስ ነው አእላፋት መላእክት ያከብሩታል ተመስገን እያሉ ይሰግዱለታል ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ዛሬ ነው የደስታ የምሥጋናችን ቀን መርገምን አርቆዋል ሰርታል ስራችንን በፍፁም ፈቃዱ እንዲሁ አድኖናል ስገድትም ምሥጋናም ለእርሱ ያንስበታል ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያው የሁሉ ፍጻሜ መጨረሻው የሚመጣው ንጉሥ ኢየሱስ ነው የዓለምን ሃጥያት ያስወገደው ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ባባቱ ቀኝ ላለው ለጌታ ለኢየሱስ አምልኮ ዝማሬ ከልባችን ይፍሰስ በክብር ታጅቦ በደመና ይመጣል ያለም ፍጥረት ሁሉ ለክብሩ ይሰግዳል ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት በዙፋኑ ላለው ክብር እንስጠው ይገባዋል ስግደት እናክብረው በምሥጋና ዜማ በዕልልታ በፊቱ እንዘምር በደስታ ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት