ከምናስበው ከምንገምተው ክምናውቀውም በላይ ነው እግዚአብሔር እርሱ ድንቅ ነው ማን ይመስለዋል እርሱ እግዚአብሔር ነው ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ነው ከእርሱ በፊት አምላክ አልተሰራም ከእርሱ በሃላም ማንም ዓይኖርም ከእግዚአብሔር ሌላ የሚያድን የለም ባሕርን ከፍሎ መንገድ ያደርጋል በምድረ በዳ ከአለት ውኃ ያፈልቃል በደረቅ በርሃ መናን ይመግባል ሸለቆውንም ውኃ ይሞላል እርሱ ኤልሻዳይ ነው ሁሉን ይችላል ምድርና ሞላዋን በቃሉ ፈጥራል ከዋክብቶችን በስማቸው ይጥራል የጸጉራችን ቁጥር በእርሱ ተቆጥራል ልብን ኩላሊትን ይመረምራል እግዚአብሔር ታላቅ ነው እርሱ ሁሉን ያውቃል እግዚአብሔር ብቻውን እርሱ አምላክ ነው እንደርሱ ያለ የለም እግዚአብሔር ልዪ ነው ክሰው አእምሮ ከዕውቀቱ በላይ ነው በምድር በሰማይ የተፈራ ነው ከሁሉም ነገር በላይ ነው