Song Lyrics

ብርሃን ነው ኢየሱስ

Netsanet Assefa
Eyesus Fikir
ብርሃን ነው ኢየሱስ ብርሃን ነው ብርሃን ነው ኢየሱስ ብርሃን ነው ጨለማን ያበራል ኢየሱስ ብርሃን ነው በጨለማ ላለ ብርሃን ነው ለተጨነቀ ሕዝብ መጽናናት ነው ከሃጥያት የሚያድን ኢየሱስ ነው እውነትና መንገድ ሕይወትም ነው ለተጠማ የሕይወት ውኃ ይሰጣል በእርሱ የሚታመን መች ይራባል ዘላለም ከእርሱ ጋራ ይኖራል ባባቱ ቤት መሰማሪያ ያገኛል በእርሱ የሚያምኑ ይድናሉ ከሃጥያት በደሙ ይነጻሉ የዘለዓለም ሕይወት ይወርሳሉ ከእርሱ ጋራ አብረው ይከብራሉ ኢየሱስ ቅርብ ነው ይገኛል የሚፈልገው ልብ ደስ ይሰኛል ሸክምን ያራግፋል እረፍት ያሰጣል አእምሮና ልብን ያስርፋል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection