ሰማይ አምላክ የሰራዊት ጌታ ነፍሴ ታመስግንህ ጥዋትና ማታ ቅኔ ልቀኝልህ ልቅረብ በዝማሬ በአንተ ስራ ነው እዚህ ያለሁት ዛሬ ዋጋ ያልነበረኝ ከንቱ የተረሳሁ አምላኬን የማላውቅ ነበርኩ እረኛ ያጣሁ በከበረው ልጅህ በደምህ ገዝተኸኝ አምላኬ ሆንክልኝ ልጅህ አደረከኝ መች አምላኬ ብቻ አበቴም ወዳጄም አስተማሪዬም ነው ጠባቂ እረኛዬም ሳዝን አጽናኜ ነው ሳጠፋም ቀጪዬ በመንገዴ ሁሉ ብርሃኔ መሪዬ ሞገሴም ነው ክብሬ ዕውቀቴ ጥበቤ መብራቴ ነው ለኔ ሆኖ ካጠገቤ ቢያመኝ መድሃኒቴ ወዜም ደም ግባቴ ኢየሱስ ነው ለኔ ዋስትና ለሕይወቴ የድህንነት ዋጋ ለኔ የከፈለው ውድ ነው ክቡር ነው ከሁሉ በላይ ነው መቼ በዚህ ብቻ ተወኝ የእኔ ጌታ ለሥጋም ለነፍሴም ሆነልኝ እርካታ