Song Lyrics

ኢየሱስ ፍቅር ነው

Netsanet Assefa
Eyesus Fikir
ቀማኛ ረብሸኛ ሌባ ተንኮለኛ ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ እብሪተኛ ኃይለኛ የፍቅር አባት ጋር ኢኢየሱስ ጋር ሲደርስ ልቡ ይማረካል ይረታል በኢየሱስ ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል ሌባውን ታማኝ ያደርጋል ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል ረብሸኛን ሰላማዊ ያደርጋል አዝ፦ ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል ብዙ ተመሬያለሁ የሚለኝ ሁሉን ቻይ ዓለም ምን እንደሆን እኔ አውቃለሁኝ ባይ የጥበብን መሰረት ጌታን ያገኝና አምላኩን ይፈራል ዕውቀቱን ይረዳና ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል ትዕቢተኛን ትሁት ያደርጋል (2x) አዝ፦ ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ይማርካል ተስፋ የቆረጠው በሰው የተናቀው ታናሽ የተባለው ዕውቀትም የሌለው የዕውቀትን ሚስጥር ኢየሱስን አግኝቶ ሩቁን ማየት ችላል ማስተዋል ተሞልቶ ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል የተናቀውን ከፍ ያደርጋል ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል የተናቀውን ያስከብራል አዝ፦ ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል የጐደለኝ የለም ሰላማዊ ሰው ነኝ ተኛለሁ እረፍት አለኝ ደህና አለኝ ደስታ አለኝ ሲል የኖረው ሀብታም ሲያደርግ እራሱን ደግ ተረዳው በኢየሱስ መሆኑን የጠፋ በግ ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል ወደ ቤትም ያስገባል (2x) አዝ፦ ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል ሸባው በአልጋ ወድቆ በበሽታ ማቆ ቆሞ መሄድ ችሏል ኢየሱስን አውቆ የሞተው ተንስቷል የእውሩም ዓይን በርቷል እርሱ ሁሉን ይችላል ታሪክ ይለውጣል ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል ሽባውንም ያራምዳል ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል የሞተውን ያስነሳል አዝ፦ ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection