Song Lyrics

ማዳኑን አይቻለሁ

Netsanet Assefa
Eyesus Fikir
ከክፉው ካስፈሪው ኢየሱስ ታድጐኛል ከጨለማ አውጥቶ ብርሃን ሆኖልኛል በጠላቴም ፊት ዘይት ቀብቶኛል ከሳሼን ጥሎልኝ እኔን አክብሮኛል አዝ፦ ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (2x) ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (2x) ሆኖልኛልና ከሰማይ በባዕድ አገር ወገን አባት ሆኖልኛል በአለቆችም ፊት ሞገስ ሆንልኛል ወንዙን ማዕበሉን እርሱ አሳልፎኛል በዚህ ክፉ ዘመን ጥላ ሆንልኛል አዝ፦ ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (2x) ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (2x) ሆኖልኛልና ከሰማይ ሥሙ እንደሚፈስ ዘይት ሆኖልኛል ልቤን በደስታ አፌን በሳቅ ሞልቷል ሕጉ ለእግሬ መብራት ብርሃን ሆኖልኛል እንዳልሰናከል ኢየሱስ ጠብቆኛል አዝ፦ ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (2x) ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (2x) ሆኖልኛልና ከሰማይ ምህረት ቸርነቱ ፍቅሩ እኔን ከቦኛል የማዳኑ ሥራ እጅግ በዝቶልኛል ስተኛ ቀስቅሶኝ ስዝል ደግፎኛል አለቱ ኢየሱስ በእጁ ይዞኛል አዝ፦ ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (2x) ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (2x) ሆኖልኛልና ከሰማይ ለውለታው ሁሉ ምን እመልሳለሁ ባወራው ባወራው አያልቅም ብዙ ነው በሕይወት ዘመኔ ለእርሱ ዘምራለሁ ተመስገን እያልኩኝ እቀኝለታለሁ አዝ፦ ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (2x) ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (2x) ሆኖልኛልና ከሰማይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection