እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳ ሁለ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊልነውና (የማቲዎስ ወንጌል ምህራፍ ፲፩ ፮ ) ያላሸከመከኝን እንዳልሸከም ከብዶኝ አንገዳግኝ እንዳልደክም ያላሳየኸኝን አይቼ እንዳልቆም ግራ ተጋብቼ ያልሰጠኸኝንም ወስጄ እንዳልቀር ኋላ ባዶ እጄን የላደረከኝንም ሆኜ እንዳልቀል በአንተ ተመዝኜ ትሁቱ ከአንተ መማር እፈልጋለሁ ታዘኸውን እግዚአብሔርን ደስ እንዳስኘኸው ትሁቱ ከአንተ መማር እፈልጋለሁ ታዘኸውን እግዚአብሔርን ደስ እንዳስኘኸው አስተምረኝ ኢየሱስ መንገድህን አንተን ተክትዬ መራመድን እኔ ትሁት ነኝ ከኔ ተማሩ እንዳልክ እሺ አስተምረኝ አንተ እንደፈልክ ስታዘኝ ሳልታዘዝህ ቀርቼ እንዳልገኝ ለጠላቴ ተመችቼ ስጠራኝ ድምጽህን ሳላውቀው ለይቼ እንዳልጠፋ በክፉው እጅ ተነድቼ ባስቀመጥከኝ በስፍራዬ ሳልቀመጥ እንዳታጣኝ በቦታዬ ስትገለጥ በሰጠኸኝ በመክሊቴ ሳላፈራ እንዳትመጣብኝ የአንተን ስራ ሳልሰራ በፈቃዴ በስሜቴ እየኖርኩኝ ጌታ እንዳልስት የአንተ ፈቃድ ነው እያልኩኝ የቆምኩኝ መስሎኝ ሳልቆም የቀረሁ እንዳልሆን እንዳልወድቅ ኋላ ልጠንቀቅ አሁን አለሁ እያልኩኝ በቤትህም እኖራለሁ ውጭ እንዳልሆን ጌታ ሆይ እፈራለሁ ዛሬ ብገኝ በአንተ ወደ አምላክ ቀርቤ እንዳልዘነጋው በአንተ መሆኑን መታሰቤ ትሁት የአንተን ቀንበር እሸከማለሁ ልዝብ ነው በእርሱ ማረስ እቻላለሁ ትሁት የአንተን ቀንበር እሸከማለሁ ልዝብነው በእርሱ ማረስ እቻላለሁ አንተን ተክትዬ መራመድን እኔ ትሁት ነኝ ከኔ ተማሩ እንዳልክ እሺ አስተመረኝ አንተ እንደፈልክ አንተ ምራኝ አንተው መዳን እንደሆንከኝ ፍጻሜዬን አንተው አሳምርልኝ እንዳረከኝ ብቻ እንዳልከኝ አድርገኝ ሁልጊዜ በአንተ ውስጥ ኢየሱስ ሰውረኝ አንተ እዘዘኝ አንተ ብቻ በኔ ስራ እኔም ከፈቃድህ ልስማማ ከአንተ ጋራ ይስማማኛል ልዝብ ነው ቀንበርህ አሸከመኝ ቀሊል ነው የአንተ ሸክምህ ትሁቱ የአንተን ሸክም እሸከማለሁ ቀሊል ነው በእርሱ መሄን እችላለሁ ትሁት የአንተን ሸክም እሸከማለሁ ቀሊል ነው በእርሱ ማሄድ እችላለሁ አስተምረኝ ኢየሱስ መንገድህን አንተን ተክትዬ መራመድን እኔ ትሁት ነኝ ከኔ ተማሩ እንዳልክ እሺ አስተመረኝ አንተ እንደፈልክ አያስኬድም ሌላው ፈጽሞ አይመችም የሚያስቆም ነው ወደፊት አያራምድም አይስማማም ፍፁም አይሰጥም ደስታ ባዶነት ነው ከንቱ ያለ አንተ ጌታ ማትረፍ የለም መክሰር ነው በጉዞዬ የለአንተ ግቡ አይደርሥም አላማዬ እንተ እንዳልክ ከአንተ መማርን መርጣለሁ ስታደርገው እያየሁ አከብርሃለሁ ትሁቱ ከአንተ ልማር እሺ እላላሁ በአንተ ላይ አርፌ መጉዋዝን እሻለሁ ትሁቱ የአንተን ቀንበር እሸከማለሁ ልዝህብ ነው በእርሱ ማረስ እችላለሁ ትሁቱ የአንተን ሸክም እሸከማለሁ ቀሊል ነው በእርሱ መሄድ እችላለሁ