Song Lyrics

ምሥጋና

Netsanet Assefa
Egziabherin Barki
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ለአንተ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ለአንተ ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ ዝማሬ ለአንተ ዝማሬ ሙገሳ ሙገሳ ሙገሳ ለአንተ ሙገሳ ሰማየ ሰማያት ለአግዚአብሐር ምሥጋና በአርያምም ለእግዚአብሔር ምሥጋና ሰራዊቱ ሁሉ ጌታን አመስግኑት ጽሀይና ጨረቃም እርሱን አመስግኑት ክዋክብትና ብርሃን እርሱን አመስግኑት የሰማያት በላይ ውሃም አመስግኑት እርሱ ብሏልና ሁኑ እነርሱም እርሱ አዞአልና ተፈጠሩም ሃሌሉያ እግዚአብሔር ይመስግን እግዚአብሔርን ከሰማይ አመስግኑት እግዜአብሔርን ከምድር አመስግኑት የእግዚአብሔርን ስሙን አመስግኑት የምድር ነገሥታት አህዛብም ሁሉ አለቆችና ፈራጆች ሁሉ ጐማሶችና ቆነጃጅቶች አመስግኑት ሽማግሌዎች ልጆች ሥሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏል ምሥጋናው በሰማይ እና በምድር ሆኗል የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል ለእግዚአብሔር ሥም ምሥጋና ይገባል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection