ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ሃጥያትሽ ይቅር ብሏል ደዌሽንም ፈውሷል ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ነፍሴ በምላክሽ ደስ ይበልሽ ነፍሴ በእግዚአብሔር ደስ ይበልሽ አምላክሽ ጠርቶሻልና ስለአንቺም ይዋጋልና ነፍሴ ባምላክሽ ደስ ይበልሽ ከዘመናት በፊት ጌታ አስቦሻል በዘለዓለም ፍቅሩ አምላክሽ ወዶሻል በገዛ ልጁ ደም ራሱ አቅርቦሻል አሜን ብይ ኃጢአትሽ ተሰርዮሻል የዚህ ዓለም ገዢ ውጊያ ቢያበዛብሽ መንግድሽን ሊያጠብ ዙሪያሽም ቢዚሮሽ በአምላክሽ ታመኚ ስለአንቺ ይዋጋል የሰራዊት ጌታ በፊትሽ ይሄዳል በልጁ የዋጀሽ ጌታሽ ካንቺ ጋር ነው ኃይለኛው እግዚአብሔር አምላክሽ እርሱ ነው በድካሙ ያፈራሽ ጽድቅሽ ኢየሱስ ሆኗል በወደድሽ በእርሱ ምህረት አግተሻል ስለአንቺ መስቀል ላይ ሁሉን ተሸክሞአል ስራውን ጨርሶ ተፈጽመ ብሏል ተንሽ አመስግኚው ምህረትሽን ውሰጂ ለዘለዓለም አምላክ ለኢየሱስ ስገጂ