ኦ የድል አምላክ ነህ ኦ ጌታ ኢየሱስ ኦ በክብር ያለህ ኦ የጽድቅ ንጉሥ ኦ ታላቅ ማዳንን ኦ አርገሃልና ኦ ለስምህ ይሁን ኦ ክብር ምሥጋና ሁሉን የምትገዛ የሁሉ ጌታ ነህ ኢየሱስ ሆይ ጽድቅና እውነት ነው መንገድህ በላይም በሰማይ ከፍ ያለ ነው ስምህ ስራህ ታላቅና ድንቅ ነው በምድር የምይፈራህ ማን ነው ስምህን ያማያከብር ስለበደላችን በደዌ የደቀቀው ስለሃጥያታችን መሰዋእት የሆነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእጁ ያከናወነው ኢየሱስ ከነፍሱ ድካም ብርሃንን ያያል ብዙዎችን አጽዶቆ እጅግ ደስ ይለዋል መጽሐፉን ዘርገተህ ማኅተሞቹን ልትፈታ ይገባሃል ኢየሱስ እል የነሳህ ጌታ ክብር ለአንተ ነው ሁሉን ስለረታህ አህዛብም ሁሉ በፊትህ ይሰግዳሉ ለስምህም ክብር ይዘምራሉ ታላቅ ክብሩን ትቶ ዝቅ ዝቅ ያለው ራሱን በአምላኩ ፊት ባዶ ያደረገው እስከመስቀልም ሞት የታዘዘው ኢየሱስ ትንሳኤ ነው ከፍ ከፍ ብሏል ባባቱ ቀኝ አለ በክብር ይመጣል