Song Lyrics

እንደሰው አይደለም

Netsanet Assefa
Egziabherin Barki
እንደ ሰው አይደለም እርሱ ሁሉን ይችላል እንደ ሰው አይደለም እርሱ ሁሉን ይችላላ እንደ ሰው አይደለም እግዚአብሔር ሁሉን ይችላል እንደ ሰው አይደለም እግዚአብሔር ሁሉን ይችላላል ሃጥያትን እግዚአብሔር ይቅር ይላል ከዓመጻም እርሱ ያነጻል ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው ምህረቱ ግን ለዘለዓለም ነው እርሱ ይሁን ያለው ይሆናል ምድርና ሞላዋን እርሱ ፈጥራል ለእግዚአብሔር የለም የሚሳነው ኤልሻዳይ አምላክ ሁሉን ችይ ነው በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ አንዳች የማይታጣው ነው ብርቱ እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው አይደክምም እርሱ አይታክትም ማስተዋሉም አይመረመርም እርሱ እግዚአብሔር ፊተኛ ነው በኋለኞችም ዘንድ የሚኖር ነው የእስራኤል ፈጣሪ ቅዱስ ነው እግዚአብሔር እርሱ ንጉሥ ነው ሥልጣን አለው ይምራል ይፈረዳል ያነሳል ይሾማል ያከብራል ለሰው የማይቻል ለእርሱ ይቻላል እግዚአብሔር ሁሉ ይቻለዋል ይራራል ይወዳል ይባርካል ይጠራል ይለያል ይልካል ከእርሱ በፊት አምላክ አልነበረም ከእርሱ በኋላም ማንም ዓይኖርም እግዚአብሔር እርሱ እግዚአብሔር ነው የሚያድን አምላክ እርሱ ብቻ ነው ያደርጋል በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛ ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ይዋጋል ይረታል ያሸንፋል በዙፋኑ ዘለዓለም ይኖራል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection