Song Lyrics

ጌታ ለእኔ ያደረከው

Netsanet Assefa
Egziabherin Barki
ጌታ ለኔ ያድረከው ልቆጥረው አልችልም ወለታህ ብዙ ነው ኢየሱስ ስለወደድ እወድሃለሁኝ አከብረሃለሁኝ ተመስገን እያልኩኝ ሳላውቅህ አውቀኸኝ ሳልወድህ ወድኸኝ በምረትህ ከበህ ቤትህ አኖርከኝ ከነፍሴ ምሥጋና ለአንተ እሰዋለሁ ምህረት ቸርነትህን እናገራለሁ በዘመኔ ሁሉ አንተን አከብራለሁ አልታዘዝም ስል በደሌን ታግሰህ በፍቅርህ ገመድ ወዳንተ መልሰህ ስወድቅ አንስተኸኝ ስዝልም ደግፈህ እዚህ አደረሰከኝ ጌታ ምን ልበልህ የሚመስልህ የለም ኢየሱስ ፍቅር ነህ ለዘለዓለምም የማትተወኝ በዘለዓለም ፍቅርህም የወደድከኝ ጌታ ኢየሱሴ የነፍሴ እረኛ ወዳጄ ነህ ለኔ የማትተኛ የማትለየኝ ስነቃም ስተኛ አትለዋውጥም ሁልጌዜ ታማኝ ነህ ፈጥነህ ትደርሳለህ ስምህን ለሚጠሩህ ኢየሱስ አምባዬ ለኔ መጠጊያዬ ዞሮ መግቢያዬ ነህ መሸሸጊያዬ ከመከራ ሁሉ መዳኛዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection