የሚመስልህ የለም አንተ እግዚአብሔር ነህ የሚመስልህ የለም አንተ ድንቅ ነህ የሚመስልህ የለም አንተ እግዚአብሔር ነህ የሚመስልህ የለም አንተ ልዩ ነህ ምህረትህ ብዙ ነው ከሕይወት ይሻላል ፍቅርህም ጥልቅ ነው እንደሞት ይበረታል ትዕግሥትህ ታላቅ ነው ዘመናት ያልፋል እግዚአብሔር ድንቅ ነህ ማን ይመስልሃል በዘለዓለም ዙፋን በክብር ተቀምጠሃል እግዚአብሔር ብርሃን ነህ ብርሃንን ለበሰሃል በቃልህ ሰማይን ምድር ፈጥረሃል ኤልሻዳይ አምላክ ነህ ሁሉ ይቻልሃል ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ አንተ ብቻ ነህ ምድርና ሞላዋን ተመለከታለህ ከቅዱስ ማደሪያ ትህዛዝ ትሰጣለህ ፍጥረትን በሙሉ አንተ ትገዛላህ ሰማይት ክብርህን ይናገራሉ ፍጥረታት በሙሉ ድምጽህን ይሰማሉ ለቃልህ በፍርሃት ይታዘዛሉ ክብርን በሙሉ ለአንተ ያመጣሉ እግዚአብሔር አንተ የለም የሚመስልህ እጅግ ከፍ ያልክ ነህ በግርማ ሞገስህ ሰው በኢየሱስ ብቻ አንተን ይቀርብሃል በእውነት በመንፈስ ደግሞ ይሰግድልሃል