Song Lyrics

ጌታ ኢየሱስ

Netsanet Assefa
Egziabherin Barki
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ የሰማይ የምድር ንጉሥ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ የፍጥረታት ሁሉ ንጉሥ ሥሙ ክብር አለው ሥሙ ክብር አለው ሥሙ ክብር አለው ሥሙ ክብር አለው ከመጀመሪያው ያለ የሁሉ መሰረት የሆነ በሰማይም በምድርም ሥሙ እጅግ የገነነ በእግዚአብሔር መላዕክቶች ፊት ታማኝ ነው የከበረ ዙፋኑ ዘለዓለማዊ በቅድስናው ያማረ በእግዚአብሔር መላዕክቶች ፊት ታማኝ ነው የከበረ ዙፋኑ ዘለዓለማዊ በቅድስናው ያማረ በወርቅ መቅረዞች መሃል በክብር ያሚመላለስ ድምጹ እንደ ብዙ ውሃዎች ድምጽ እግሮቹ እንደነጠረ ናስ ደረቱን በወርቅ ታጥቋል ዓይኖቹ የእሳት ነበልባል ከአፉ ስይፍ ይወጣል ፊቱ አንደ ፀሐይ ያበራል ደረቱን በወርቅ ታጥቋል ዓይኖቹ የእሳት ነበልባል ከአፉ ስይፍ ይወጣል ፊቱ አንደ ፀሐይ ያበራል መጽሐፊንፉንም ሊወሰድ መሐተሞቹን ሊፈታ የገባዋል ኢየሱስ የጌቴች ሁሉ ጌታ ለእግዚአብሔር አዲስ ሕዝብን በደሙ ስለዋጀ መንግሥትና ካህናት ለአምላኩ አዘጋጀ ለእግዚአብሔር አዲስ ሕዝብን በደሙ ስለዋጀ መንግሥትና ካህናት ለአምላኩ አዘጋጀ ለወደደን በደሙ ከኃጢአታችን ላጠበን ለአምላኩ መንግሥትና ካህናት ላደረገን በክብር ለሚመጣው ኃይል ለእርሱ ይሁን እሰከዘለዓለም ድረስ ክብርም ለእርሱ ይሁን በክብር ለሚመጣው ኃይል ለእርሱ ይሁን እሰከዘለዓለም ድረስ ክብርም ለእርሱ ይሁን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection