Song Lyrics

ውለታው አምላኬ

Netsanet Assefa
Alegn Bizu Misgana
ውለታው አምላኬ ለኔ ያደረገው አያልቅም ባወራው ከእምሮ በላይ ነው ተመስገን ልበለው በምድር ላለው ለእንዳዱ ሰው ግድ የተሰኘው ራሱን ለዓለም ቤዛ አድርጐ እንዲሁ የሰጠው ለጠሉትና ላልተቀበሉት ሆኖ መስቀል ላይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቀር በል አባት ሆይ ያለው ይሄ ጌታ ምን ዓይነት ፍቅር ነው ምንስ ዓይነት ቋንቋ ይችላል ሊገልጸው በምድር ካሉ ከተዋረዱ ከድሆች በላይ ኢየሱስ ስለእኛ ቤዛ ሆነልን መጥቶ ከሰማይ የሁላችንን በደልና ኃጢአት ተሸከመልን እዳችንን እርሱ ከፍለ ነጻም አወጣን በፍፁም ልባችን ጌታን ብንወደው አይገባውም ወይ ለእኛ ላደረገው መች በዚህ ብቻ በዚህ አበቃ የኢየሱስ ፍቅር ከእርሱ ጋራ ወራስህ አረገን አብሮን የምኖር የእርሱ የሆነውን አንዳችም ሳይቀር ለእኛ ሰጠው ባርኮቱን ሁሉ ምንም ሳይሰስት ለእኛ አፈሰሰው ታዲያ ለዚህ ጌታ ለእርሱ ብኖርለት ይገባዋል እንጂ መች በዛበት ይህንን ውለታ የዋልልን ኢየሱስ ይመጣል በዚህች ምድር ላይ ናፍቀን እንቀርም መጥቶ ይወስደናል ወዳችንን በዓይናችን እናዋለን ወድቀን ከእግሩ ስር እንወድሃለን እንለዋለን ከተስፋ ሁሉ በላይ የተባረከው ተስፋችን ጌታ ኢየሱስ ነው ስናየው ባይናችን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection