Song Lyrics

የሚያስፈልገኝን ያውቃል

Netsanet Assefa
Alegn Bizu Misgana
የሚያስፈልገኝን እርሱ ያውቃል የሰማይ አባቴ ለኔ ያስባል እጆቼን ወደ እርሱ ዘረጋለሁ በዘለዓለም አምላክ እታመናለሁ የሚያስጨንቀን በእርሱ ጥዬ እታመናለሁኝ በጌታዬ ጽድቁና መንግሥቱን እሻለሁኝ ክብሩን እያየሁኝ እጠግባለሁኝ ላመልከው ብቻ ነው የፈጠረኝ ከእርሱ ሌላ ምንም ላይገዛኝ እያሞጋገስኩኝ ታላቅ ስሙን አመልከዋለሁኝ እግዚአብሔርን የጠራኝ የለየኝ የቀደሰኝ ለእርሱ ካህን ልሆን ነው የቀባኝ እርሱ ያደረገኝ እሆናለሁ የኣምላኬን በጐነት አወራለሁ መልካሙን ስራውን የጀመረው የጠራኝ እግዚአብሔር ታማኝ ነው እስከ ክርስቶስ ቀን ሊፈጽመው ይችላል አምላኬ ታማኝ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection