ኢየሱስ ለኔ ሁሉን ነው ጌታዬ እርሱ በቂ ነው የሚያሻን የለም ጌታ አለኝ ሁሉ በሁሉ የሆንልኝ ምን ያሻኛል ምን ያሻኛል ምን ያሻኛል ጌታ ይበቃኛል ምን እሻለሁ ምን እሻለሁ ምን እሻለሁ ጌታን እግኝቻለሁ የሰማይ የምድር ጌታ በኃይሉ እጅግ የበረታ ኢየሱስ ነው ለኔ የተሰጠኝ በረከት ሙላት የሆንልኝ ብሩና ወርቁም የእርሱ ነው አምላኬ ሁሉን የፈጠረው እንደ ፈቃዱ የሆነው የአባቴ ፈቃድ ለኔ ነው የእርሱ የሆነው የእኔ ነው ወራሽ ነኝ ጌታ አባቴ ነው እንደ ባሪያ ሳሆን እንደ ልጅ ተቀብሎኛል እንደ ወዳጅ ለዚህ ጌታ እዜማለሁ በመንፈሥም እቀኛለሁ ለእርሱ ክብር ለእርሱ ምሥጋና ይኸው መዝሙር ታላቅ ነውና