Song Lyrics

አሳረፈኝ

Netsanet Assefa
Alegn Bizu Misgana
የእኔ ነሽ ብሎ አሳረፈኝ የእኔ ነሽ ብሎ አሳረፈኝ የእርሱ አድሮጐኛል ጌታዬ አሳርፎኛል የእርሱ አድሮጐኛል አሳርፎኛል ሃሳቤን ሁሉ ወዲያ ትቼ ለአላማህ ተነስቼ በጐነትክን ጽድቅህን ላውራ አንተ አለህ ከኔ ጋራ እንደኔማ እንደ ሃሳቤ አመስገኜ መች ጠገቤ ከእንግዲህ የምኖረው ለሞተልኝ ለእርሱ ነው ማን ነው ከእርሱ በቀር ነገን የሚያውቀው ትንፋሼን መንዴን እርሱ የያዘው እግዚአብሔር የሰራት ይህቺ ቀን ዛሬ ናት በእርሱ ደስ እያለኝ ሃሴት ላድርግባት ግሩምና ድንቅ አድርጐ ፈጥሮኛል በፈጥረኝ አምላክ እጅግ ደስ ይለኛል ግሩምና ድንቅ አድርጐ ፈጥሮኛል በፈጠረኝ ጌታ እጅግ ደስ ይለኛል እኔ በእግዚአብሔር ደስ እሰኛለሁ እኔ በፈጣሪዬ ደስ እሰኛለሁ እኔ በመድሃኒቴ ደስ እሰኛለሁ እኒ በእግዚአብሔር ደስ እሰኛለሁ የእኔ ነሽ ብሎ አሳረፈኝ የእኔ ነሽ ብሎ አሳረፈኝ የእርሱ አድሮጐኛል ጌታዬ አሳርፎኛል የእርሱ አድሮጐኛል አሳርፎኛል እርሱ ይሁን ብሎ በፈጠራቸው እራሱ እይቶ መልካም ባላቸው አምላኬ ፍቅሩ በዚህ አለበቃውም የልቡን ሃሳብ አልገለጡትም ፍቅሩን ለኔ እንዲህ ገለጠ ሃሃ ራሱን መባ አድርጐ ስለኔ ሰጠ አምላክ ሰው ሆኖ ምድር መጣና ሃሃ የእርሱ አደርገኝ ሞተልኝና እኔ በእግዚአብሔር ደስ እሰኛለሁ እኔ በፈጣሪዬ ደስ እሰኛለሁ እኔ በመድሃኒቴ ደስ እሰኛለሁ እኒ በእግዚአብሔር ደስ እሰኛለሁ በፈቴ ያለውን ተራራ እያየሁኝ ረዳት እንደሌለው ምን ተስፋ አስቆረጠኝ ተራራን የሰራ ረዳቴ ይመጣና መንገድ ያደርግልኛል ሜዳ ሁን ይልና እርሱ አማኑኤል ከእኔ ጋር ነው እግዚአብሔር እያለ መተከዝ ምንድ ነው እርሱ አማኑኤል ከእኔ ጋር ነው እግዚአብሔር እያለ መተከዝ ምንድ ነው የእኔ ነሽ ብሎ አሳረፈኝ የእኔ ነሽ ብሎ አሳረፈኝ የእርሱ አድሮጐኛል ጌታዬ አሳርፎኛል የእርሱ አድሮጐኛል አሳርፎኛል ምህረት ቸርነቱን ፍቅሩን አይቻለሁ ለሚታመኑበት መከታ ጋሻ ነው አስተማማኝ አምባ እረኛ እርሱ ነው መንጋዎቹን ከእጁ የማይነጠቀው ደስ ይበለኝ እንዲ በዚህ ታላቅ ጌታ ደስታን ባስታጠቀኝ በሰቆቃ ፈንታ ሕይወትን በሰጠኝ ሞቶ በኔ ፈንታ እኔ በእግዚአብሔር ደስ እሰኛለሁ እኔ በፈጣሪዬ ደስ እሰኛለሁ እኔ በመድሃኒቴ ደስ እሰኛለሁ እኒ በእግዚአብሔር ደስ እሰኛለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection