Song Lyrics

አሸናፊ ነው

Ashenafi New

እግዚአብሔር ተዋጊ ስሙ እግዚአብሔር ነው በዘመናት መሃል ተፈርቶ የኖረው የተሰወረውን ሚስጥር የሚገልጥ በሃይልና ብርታት ከሁሉ የሚበልጥ አሸናፊ ነው የኛ ጌታ አሸናፊ ነው ሁሉን ሚረታ አሸናፊ ነው ክንደብርቱ ማብቂያ የሌለው ለመንግስቱ ባለግርማ የተፈራ ቀኙ በሃይል የከበረ ሁልግዜ እየረታ እያሸነፈ የኖረ የተነሱበትን ቀጪ ቁጣውን እየሰደደ በሰማይ በምድር የለም ደፍሮት በደህና የሄደ አሸናፊ ነው የኛ ጌታ አሸናፊ ነው ሁሉን ሚረታ አሸናፊ ነው ክንደብርቱ ማብቂያ የሌለው ለመንግስቱ ከግብፃዊያን ምድር ህዝቦቹን ያወጣ ያስገበራቸውን ፈርዖንን የቀጣ የሰራዊት አምላክ ገናና ስመኛ ክንዱን የሚሞክር የለው ወደረኛ የሰራዊት አምላክ ገናና ስመኛ ክንዱን የሚሞክር የለው ወደረኛ የማይመረመረውን ድንቅ ታላቅ ነገር ሰሪ ሁሉ የሚታዘዙለት የሌለው ተከራካሪ ወደሱ ሮጠው ለመጡ የሚያስጠልል ነው መሸሻ ቅጥርን አዘላይ መከታ ለታመኑት የሚሆን ጋሻ አሸናፊ ነው የኛ ጌታ አሸናፊ ነው ሁሉን ሚረታ አሸናፊ ነው ክንደብርቱ ማብቂያ የሌለው ለመንግስቱ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection