Song Lyrics

ቶሎ ና

Tolo Na

አቤት የአምላክ ፍቅር ለሰው ልጅ የሳየው እጅግ የበረታ ታላቅ ሃይለኛ ነው አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ እንዲሁ ወደደን ከፍርድ እንድናመልጥ አቤት የሱስ ፍቅር ለሰው ልጅ የሳየው እጅግ የበረታ ታላቅ ሃይለኛ ነው አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ እንዲሁ ወደደን ከፍርድ እንድናመልጥ እግዚአብሔር የሰውን ልጆች ከሰማይ ጠራ ለደባበተው ለጨለመበት ብርሃን አበራ ወደዚህ ግብዣ የሚያስገባው ወልድ እሱ ብቻ የህይወትን በር የዘላለሙን ያለው መክፈቻ ቶሎና ወደዚ እውነት ቶሎና ሊሆንህ እውነት ወንድሜና ይፈልግሃል ቶሎና ያሳርፍሃል ውሉዋን የማትጠብው አስጎምዥታ ነሺ ደስታው አይበረክት አለም ከንቱ ጠፊ በጥም ለደረቀ ምድረበዳ አዳሪ ምንጩ እየሱስ ነው ዘላለም አኗሪ እግዚአብሔር የሰውን ልጆች ከሰማይ ጠራ ለደባበተው ለጨለመበት ብርሃን አበራ ወደዚህ ግብዣ የሚያስገባው ወልድ እሱ ብቻ የህይወትን በር የዘላለሙን ያለው መክፈቻ ቶሎ ነይ ወደዚ እውነት ቶሎ ነይ ሊሆንህ እውነት እህቴ ነይ ያሳርፍሻል ቶሎ ነይ ያስጠልልሻል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection