አንተን ተስፋ አርጌ ጸልዬ ነበረ ጸሎቴን ሰምተኻል ስለቴ ሰመረ። አንተን ተማምኜ ተስዬ ነበረ ጩኸቴን ሰምተኻል ስለቴ ሰመረ። ጸሎትን ትሰማለህ ዕንባንም ታብሳለህ። ለሚጠሩህ ቅርብ ነህ እጅህን ትከፍታለህ። አንዳንድ ጊዜ እታወካለሁ የሚነፍሰው ንፋስ ታንኳዬን ሲንጠው። መርከቤ ላይ ጌታዬ ተኝተህ ይኼ ኹሉ ሲሆን አትሰማም ወይ ነቅተህ? 'ሚኾነው ሳይገባኝ ተጨንቄ ሳምጥ ታንኳዬ በውሃ ሲሞላ ስናወጥ ማ'በል ሚታዘዝህ 'ሚሰማህ ወጀቡ በተነሳህ ጊዜ ግን ያወኩኝ ዝም አሉ ምንም ምንም አይሳንህም የማመልክህ ጌታ ትችላለህ ኹሉንም። ምንም ምንም አያቅትህም የታመንኩህ ጌታ ትችላለህ ኹሉንም። ባለመድኀኒት ያልተገኘላት ላስራ ኹለት ዓመት ደም እየፈሰሳት ተንከራታች ንብረቷንም ሰጥታ ማንም አልተገኘ ችግሯን ሚፈታ። ከሕዝብ ኹሉ መኻል በእምነት ተጋፍታ ፈውሷን ተቀበለች የልብሱን ጫፍ ነክታ። ለስንቱ መለኛ ላዋቂ ያቃተ ድንቅ መካር ኃያል ቀላል ነው ለአንተ። ምንም ምንም አይሳንህም የማመልክህ ጌታ ትችላለህ ኹሉንም። ምንም ምንም አያቅትህም የታመንኩህ ጌታ ትችላለህ ኹሉንም። ምንም ምንም አይሳንህም የማመልክህ ጌታ ትችላለህ ኹሉንም። ምንም ምንም አያቅትህም የታመንኩህ ጌታ ትችላለህ ኹሉንም።