Song Lyrics

ላመስግንህ

Lamesginih

የልቤ አምላክ ሁሉ ነገሬ እየመራህኝ ባንተ ተምሬ ከራሴ መንገድ እየመለስከኝ ማይታለፈውን አሻገርከኝ ጌታ ምረትህ እጅግ ብዙ ብዙ ነው ጌታ ምረትህ አቤት ይቅርታ እጅግ ብዙ ብዙ ነው አቤት ይቅርታ አቤት ደግነት መጨረሻ የለው ለደግነትህ ርህራሄ መጨረሻ የለው ርህራሄ ላመስግንህ እስኪ ላመስግንህ ለውለታህ ምላሽ እንኳን ባይመጥንም ላመስግነህ ውዴ ላመስግንህ ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንም ከተጠመደብኝ ወጥመድ አስመልጠህ ከክፋ ውሳኔ ልቤን እኔን ጠብቀህ ቃልህን እየላክ አባ እየመከርከኝ ከጠላቴ አጥፊው እቅድ ፈጥነህ አዳከኝ ተመስገን አባ ተመስገን ላረክል ነገር እንኳን ባይመጥንም ተባረክህ አባ ተባረክህ ለውለታህ ምላሽ ምስጋና ላብዛልህ በጭንቅ ቀኖቼ ሁሉ ከጉኔ ነህ ሰብራቴን ሳካፍልህ መቼ ደከመህ ሁሉም በተውኝ ጊዜ የትም አልሄድም በጊዜ ብዛት አይላላም ወዳጅነትህ ተመስገን አባ ተመስገን ላረክል ነገር እንኳን ባይመጥንም ተባረክህ አባ ተባረክህ ለውለታህ ምላሽ ምስጋና ላብዛልህ በምድረበዳ ሸለቆ አሰልጥነህ የጨከንክብኝ ሲመስለኝ ቀርበህ አባብለህ ሁሉ ለበጉ ሲቀየር ባየኔ እያየው ለመልካም ስላስጨነከኝ አከብርሀለው ተመስገን አባ ተመስገን ላረክል ነገር እንኳን ባይመጥንም ተባረክህ አባ ተባረክህ ለውለታህ ምላሽ ምስጋና ላብዛልህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection