Song Lyrics

ያ መሲህ

Ya Mesih

ዝቅ ብሎ መጣ አነሰ ስለኛ ክፋት እንዳረገ ወንበዴ ፍርደኛ የሰው ልጅ እርቃኑን በመስቀል ላይ ታየ በዚያ በጎለጎታ በቀራንዮ ቆየ ያ መሲህ ዝቅ አለ ያ ንጉስ ዝቅ አለ ከአብርሀም በፊት የነበረው እርሱ ሰው ሆነ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ ተዋረደ ሆነ የተጠላ ተገረፈ መከራውን በላ እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆነ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ እንዲያ ሲያናንቁት አንዳች አልመለሰም ሲዘባበቱበት ሲሰድቡት ታገሰ እጁ ባበጃቸው እጅ ላይ ወደቀ የህማም ሰው ሆነ በደዌ ደቀቀ ያ መሲህ ዝቅ አለ ያ ንጉስ ዝቅ አለ ከአብርሀም በፊት የነበረው እርሱ ሰው ሆነ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ ተዋረደ ሆነ የተጠላ ተገረፈ መከራውን በላ እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆነ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ ተንኮል የሌለበት ፃድቅ ሆኖ ሳለ ደዌአችንን ወስዶ ስለኛ ቆሰለ የሁላችን በደል በእርሱ ላይ ሆነ ነፍሱን አሳልፎ ለሞት አቀረበ የድል ንጉስ(4) እንደሞተ አልቀረም ተነስቷል ኢየሱስ መቃብሩ ባዶ ነው የኛ ጌታ ህያው ነው። መቃብሩ ባዶ ነው በዚያ የለም ህያው ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection