Song Lyrics

አትለዋወጥም

Atilewawetim

አንተ የዘመናት አምላክ ያው አንተ ነህ አንተን አትለዋወጥም ያው አንተ ነህ አንተ እኔ እኔ ነኝ ያልህ ያው አንተ ነህ አንተ ትላንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ የማትለዋወጥ አንተ ብቻ ዘመን የማይሽርህ አንተ ብቻ የነበርህ ያለህ አንተ ብቻ ዙፋንህ የፀና አንተ ብቻ ክበር ክበርልን ንገስ ንገስ ሙሉ መሰዋታችን ላንተ ይፍሰስ/3 አለም ተለዋዋጭ ሁሉ ሲቀያየች ከፍ ያለው ዝቅ ሲል የነበረው ሲቀር ፍሰቱን ጠብቆ ሁሉ ሲተካካ አንተ ፀንተህ ኗሪ ምንም አትነካ አንተ የዘመናት አምላክ ያው አንተ ነህ አንተን አትለዋወጥም ያው አንተ ነህ አንተ እኔ እኔ ነኝ ያልህ ያው አንተ ነህ አንተ ትላንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ ብርቲዎች ሲደክሙ ደካሞች ሲገዙ ሽማግሌው ሲያልፍ ሲያረጅ ጎበዙ ዕውቀትም ሲሻሻል ስልጣኔም ሲሻር አንተ ለዘላለም ተረጋግተህ ምትኖር አንተ የዘመናት አምላክ ያው አንተ ነህ አንተን አትለዋወጥም ያው አንተ ነህ አንተ እኔ እኔ ነኝ ያልህ ያው አንተ ነህ አንተ ትላንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ የማትለዋወጥ አንተ ብቻ ዘመን የማይሽርህ አንተ ብቻ የነበርህ ያለህ አንተ ብቻ ዙፋንህ የፀና አንተ ብቻ ክበር ክበርልን ንገስ ንገስ ሙሉ መሰዋታችን ላንተ ይፍሰስ/4
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection