Song Lyrics

ጉዞ ወደ ክብር

Guzo Wedekibir

አቤት ውበቱ ክርስትና የምንጠብቀው አለንና አቤት ሲያምር ክርስትና ጉዞ ወደ ፅዮን ነውና አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ መንገድህ ድንቅ ነው ጌታ ስትመራ አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ መንገድህ ልዩ ነው ጌታ ስትመራ የፅድቅ ጉዞ እንዴት ያምራል ምክር ግሳፄህ እንዴት ያምራል ማፅናናት ፍቅርህ እንዴት ያምራል ቅጣት ቁንጥጫህ እንዴት ያምራል መስቀልህን ይዞ አንተን መከተሉ ቢያምም ይጣፍጣል መታገስ በሁሉ ለድል ሰንደቅ ጉዞ ብናልፍ በመከራ ምሽቱ ሊያበቃ ጥቂት ቀርቷልና አቤት ሲያምር ክርስትና ጉዞ ወደ ክብር ነውና አቤት ወበቱ ክርስትና የምንጠብቀው አለንና አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ መንገድህ ድንቅ ነው ጌታ ስትመራ አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ መንገድህ ልዩ ነው ጌታ ስትመራ ታግሶ የሄደ ባንተ የተመራ በፀጋህ ታግዞ ጦርነት ሳይፈራ ሰልፍ ሳያስቆመው እየገሰገሰ የይሁዳ አንበሳ አንተን አነገሰ አቤት ውበቱ ክርስትና የምንጠብቀው አለንና አቤት ሲያምር ክርስትና ጉዞ ወደ ፅዮን ነውና አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ መንገድህ ድንቅ ነው ጌታ ስትመራ አንዴ በሸለቆ አንዴ በተራራ መንገድህ ልዩ ነው ጌታ ስትመራ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection