ክርስትያን የታለህ የክርስቶስ ወገን ጊዜውን ተረዳ ተመልከት ዙሪያህን ዘመኑ ተቃርቧል ሊፈፀም ትንቢቱ የንጋቱ ኮከብ መምጫው ነው ሰሀቱ የበጉ ሰርግ ስለደረሰ የነፃውን ልብስህን ለብሰ ጠብቅ በተጠንቀቅ ወገብህን ታጠቅ ሸክምን ሁሉ የከበበንን ሀጥያት አዉልቀን የሚያፀናውን የጌታችንን ፀጋ ደርበን መዳናችን ይበልጥ(አሁን) ወደእኛ ቀርቧል ከእንቅልፍ እንንቃ ለሊቱ አብቅቷል የበጉ ሰርግ ስለድረሰ የሰማዩን የመዳን ዕውነት ወንጌል መስካሪ የክርስቶስ በጎ ወታደር አዋጅ ነጋሪ ተነስተህ ተሰለፍ የቃሉን ጦር አንሳ አደራህን አድርስ ስራህን አትርሳ ተነስ ተነስ ተነስተህ ተዋጋ የቃሉን ጦር አንሳ ከዚህ አለም ገዢ ተናጠቅ ድልንሳ የበጉ ሰርግ ስለደረሰ እርቅ ሲርቅ ቂም ሲቀርብ ጥላቻ መድረኩን ይዞ አንዱ በአንዱ ላይ ሲነሳ ፍቅር እጅጉን ቀዝቅዞ የነበረው በድንገት ሲለወጥ በየስፍራው የምናየው መናወጥ ሁከት እና ረሀብ ጦርነቱ ይነግረናል መድረሱን ሰሀቱ