ከሰማየ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ ከድንግል ማርያም በበረት ተወልዶ እንደ ፋሲካ በግ ስለ እኛ ታረደ ሞታችንን ሞተው ፍዳችንም ሄደ ፍርድ ተወገደ አዎ ይወደናል አዎ ያፈቅረናል ነፍስን እስከ መስጠት ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የት አለ? ኢየሱስ ያድናል አዎን አድኖናል ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል መልካም እረኛ ነው እጅግ የሚራራ በለመለመ መስክ ሕዝቡን የሚመራ ከአብ ጋር ያስታረቀን ያረገን ዘመድ የሕይወት በር ነው እውነት ነው መንገድ አቤቱ ፍቅሩ ነው ብርቱ አቤቱ አቤቱ ብዙ ቸርነቱ አቤቱ አቤቱ ጥልቅ ነው ምህረቱ አቤቱ አቤቱ እልፍ ቸርነቱ አቤቱ የተጠላነውን እንዲሁ ወደደን ሰው ኾኖ የዓለምን ኀጢአት አስወገደ ፍቅሩ ውቅያኖስ ነው በዘመናት ኹሉ የወንጌል ማኅበራት ለእርሱ እልል በሉ ለጌታ ዘምሩ አዎ ቤዛችን ነው አዎ ተቤዥቶናል ከኀጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶ የራሱ አርጎናል ኢየሱስ ያድናል አዎ አድኖናል ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል አዎ ብርሃናችን ነው አዎ በርቶልናል ከአስፈሪው ጨለማ ከድቅድቁ ታድጎናል ኢየሱስ ያድናል አዎ አድኖናል ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል አዎ ብርሃናችን ነው አዎ በርቶልናል ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል ኢየሱስ ያድናል አዎ አድኖናል ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል