Song Lyrics

ወዳንተ እሮጣለሁ

Meskerem Getu
Special Edition
የዓለም ምናምንቴ አይስበኝም ከቶ አያምረኝም የሚያብረቀርቀው አይገዛኝም ከቶ አያታለኝም በሚያልፈው በሚጠፋው አልማልልም ከቶ አልጎመጅም ሀሳቤ ተወርሷል ባንተ በኢየሱስ ነብሴን የሚያረካት ፍቅርህ ነው በፊትህ መፍሰስ እወድሃለው ከውስጤ ከአንጀቴ አንተ ብቻ እኮ ነህ የሞላኸው ቤቴ ብዬ ብዬ አልጥግብ ስላንተ ባወራ የህይወት ውሃ ነህ የህይወት እንጀራ እራብሃለው እራብሃለው ጌታ መድኃኒቴ አንተን እሻለው እጠማሃለው እጠማሃለው ኢየሱስ መድኃኒቴ አንተን እሻለው የፀዳልህ ብርሃን ሚናፈቀው ክብርህ የልቤ ተማጥኖ እንዳየው ያን ፊትህ ምጠይቅህ የለ ከእጅህ እንድቀበል ግን እንዲያው ዝም ብዬ ከእግርህ ቁጭ ልበል ገና በማለዳ ወደ አንተ እሮጣለው የመንፈስህ እሳት ህይወቴን ያግለው ልማርህ እሻለው እንዳውቅህ አጥብቄ ከህልውናህ ጋር ልኑር ተጣብቄ ፈልግሃለው እስካገኝህ ድረስ እጣደፋለው እጠማሃለው ጌታ መድኃኒቴ አንተን እሻለው ክብሬ ነህ አዶናይ ቀኔን የምታፈካ የምትሰጠው ደስታ በምንም ማይተካ አብሮነትህ እኮ ነው ህይወቴን ያጣመ ዛሬም ልቤ አንተን አንተን ብቻ አለመ ገና በማለዳ ወደ አንተ እሮጣለው የመንፈስህ እሳት ህይወቴን ያንድደው ልማርህ እሻለው እንዳውቅህ አጥብቄ ከህልውናህ ጋር ልኑር ተጣብቄ እወድሃለው ከውስጤ ከአንጀቴ አንተ ብቻ እኮ ነህ የሞላኸው ቤቴ ብዬ ብዬ አልጥግብ ስላንተ ባወራ የህይወት ውሃ ነህ የህይወት እንጀራ እራብሃለው እራብሃለው ጌታ መድኃኒቴ አንተን እሻለው እጠማሃለው እጠማሃለው ኢየሱስ መድኃኒቴ አንተን እሻለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection