Song Lyrics

እጆችሽን ዘርጊ

Meskerem Getu
Special Edition
ኢትዮጵያ x2 እማማ ሀገሬ ኢትዮጵያ x2 ኢትዮጵያ x2 እናት ሀገር ምድሬ ኢትዮጵያ x2 ሰላም እፎይታሽን አድብቶ ሚናጠቅ ክፉ ጨካኝ አውሬ ዲያብሎስ ደም አፋሶ ሚስቅ ወንድም ከወንድሙ እያገፋተረ በትውልዱ ልብ ውስጥ አመፃን ጥላቻን ያኖረ ዛሬ በአምላክ ስልጣን ትእዛዝ ከላይ ይውጣ ጠላትሽ ይሰየፍ በጌታዬ ቁጣ ዳር ድንበር ዙሪያሽን ይጠርሽ በእሳቱ የጨለማው ምክር ይሁንበት ከንቱ ኢትዮጵያ x2 እማማ ሀገሬ ኢትዮጵያ x2 ኢትዮጵያ x2 እናት ሀገር ምድሬ ኢትዮጵያ x2 (ኢትዮጵያ) ሀገሬ እናት እናት ሀገሬ እጆችሽን ዘርጊ እናት እናት ኢትዮጵያ ኦሆሆ በምስራቅ በደቡብ በምዕራብ በሰሜኑ ልጆችሽ ጥላቸውን አዋድቀዉ በህብረት ያብሩ በህዝብሽ ላይ ይታይ ይቅርታ ውህደቱ ለቂም እምቢ ብለው በአንድነት ለፍቅር ይዝመቱ እውነት በአደባባይ ይታይ በከፍታ የሐሰት ምስክር የሚሰማው ይጣ እናቶች አባቶች ወጣት ልጆች ሁሉ ከክፋት ሸፍተው ለእርቅ ያዘንብሉ (ሀገሬ እማማ) እናት ሀገሬ ነሽ አምላክ የባረከሽ ተስፋ አደረግነው መጣልን ማለዳ ፍርዱ አልዘገየም ወረደ በቁጣ የአምላክ ፍርዱ ወጣ ወረደ በቁጣ x2 (ወረደ ሆ) x4 የሀገሬ ልጆች ቀና በሉ የደስታ ቀን ነው አትዘኑ የጸለይነውን አግኝተናል ለአስጨናቂያችን መርዶ ሆኗል ለቅሶ ሆኗል መርዶ ሆኗል ሰላም ይፍሰስ ይብዛ ይብዛ አሀሀ ንጋት ሆኗል አልፏል ማታ አሀሀ ለአማኑኤል ለንጉሡ አሀሀ የምስጋናን ከበሮ አንሱ አሀሀ አመስግኑ ሆ ከበሮ አንሱ ሆ አመስግኑ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection