Song Lyrics

ተወለደ እንደገና

Meskerem Getu
Mengistih Timta
በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው ሚያድነው (፪x) በራስህ ኃይልና ጉልበት ነፍስህን አታድንም በያዝከው ሃብትና ንብረት እርካታን አታገኝም ይልቅስ ቶሎ ብለህ : ና ትምክትህን ተውና ኢየሱስ ጌታዬ ብለህ ተወለድ እንደገና ያኔ ነው እርካታህ ያኔ ነው ፍፁም ደስታህ (፪x) በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው ሚያድነው (፪x) በመስቀል ላይ ጌታ ሲሞት እዳህን ተሸክሞ ከኃጢአት ደዌ ሊያድንህ ስለአንተ እርሱ ቆስሎ ኃጢአትህን ደምስሶልሃል ንጹህ ደሙን አፍስሶ ና ልጄ ናና ይልሃል ስራህንም ጨርሶ ድምጹን ስማ ወዳጄ ተከፍቷል የምህረት ደጄ ድምጹን ስማ ወዳጄ ተከፍቷል የምህረት ደጄ በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው ሚያድነው (፪x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection