Song Lyrics

የጌታ ውድ ልጅ

Meskerem Getu
Mengistih Timta
የመዳን ሚስጢር ትፈቶልህ ኢየሱስ ነግቶ በትላንትህ በፍቅሩ ስንቴ ተጽናንተሃል ሁሉን ትቶ ከጐንህ ቆሞልሃል ዛሬ ምን ስንፍና ተበተበህ አጥርተህ እንዳታይ ዓይንህን ከለለህ ከዘላለሙ ይልቅ ለሚያልፈው ተገኘህ ጌታን በመተውህ እንደምን ተሞኘህ አዝ፦ የጌታ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ የተበትበህን በጣጥሰህ ተራመድ ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ ብርሃንን ትተህ ወደ ጨለመበት ትገሰግሳለህ የነፍስህን ሰላም ከማታገኝበት ሰፈር ትሮጣለህ ምንስ ብትኮበልል ከኢየሱስ ፍቅር ወዴት ትሸሻለህ ለአንተ ሲል አይደል ወይ ነፍሱን የሰጠልህ በመስቀል የወለ አዝ፦ የአባቴ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ የተበትበህን በጣጥሰህ ተራመድ ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ የመዳን ሚስጢር ትፈቶልህ ኢየሱስ ነግቶ በትላንትህ በፍቅሩ ስንቴ ተጽናንተሃል ሁሉን ትቶ ከጐንህ ቆሞልሃል ዛሬ ምን ስንፍና ተበተበህ አጥርተህ እንዳታይ ዓይንህን ከለለህ ከዘላለሙ ይልቅ ለሚያልፈው ተገኘህ ጌታን በመተውህ እንደምን ተሞኘህ አዝ፦ የጌታ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ የተበትበህን በጣጥሰህ ተራመድ ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ እንዴት ሊሆን ሰበብ የአንተ መገፋት ቢነሳብህ ዱላ ይከፍል የለ ወይ ለሁሉ እንደስራው ብትታገስ ኋላ ወንድሜ ተመለስ ጌታ ነው ሚበጅህ ምን ቢበዛ ሰልፉ ዛሬም ይወድሃል ፍቅሩ አልቀነሰም ግባ ወደ እቅፉ አዝ፦ የአባቴ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ የተበተበህን በጣጥሰህ ተራመድ ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection