ሰው ሰው የሆነበት የሚኖርበት ምክንያት ካልገባው በአካል ኖረ እንጂ የነፍሱን ክፍተት በምን ሊሞላው ኑሮን ለማሸነፍ እሮጦ እሮጦ ቢደርስ ከግቡ ተሳካለት ቢባል ሃሳቡ ሞልቶ እንዲያው ለደንቡ ግን ይሄ አይደለም የሕይወት ትርጉሙ ከማግኘት ይበልጣል ለተፈለጉበት መገኘት በውሉ ሃብትን ለማካበት ከመባዘን ይልቅ ለምን እንደምንኖር በተጋን ለማወቅ አዝ፦ ለምንድነው የምንኖረው እስትንፋሳችን የሚቀጥለው ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ (2x) እርካታ በገንዘብ በመብል መጠጥ ከተገደበ በጉብዝናው ጊዜ የፈጠረውን ሰው ካላሰበ ኋላ በእድሜው ምሽት እንዳይጸጸት ከአሁኑ ይንቃ የተፈለገበትን ምክንያት ያግኝ ቀኑ ሳያበቃ በምድር ላይ ያስገኘን በሰማያት ያለ አላማ ሰጥቶናል የምንኖርብት ከቁስ በዘለለ ሁሉም በየድርሻው በተሰጠው ስራ ለመፈጸም ይሩጥ የአምላክን አደራ አዝ፦ ለምንድነው የምንኖረው እስትንፋሳችን የሚቀጥለው ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ (2x) ሰው ሰው የሆነበት የሚኖርበት ምክንያት ካልገባው በአካል ኖረ እንጂ የነፍሱን ክፍተት በምን ሊሞላው ኑሮን ለማሸነፍ እሮጦ እሮጦ ቢደርስ ከግቡ ተሳካለት ቢባል ሃሳቡ ሞልቶ እንዲያው ለደንቡ ግን ይሄ አይደለም የሕይወት ትርጉሙ ከማግኘት ይበልጣል ለተፈለጉበት መገኘት በውሉ ሃብትን ለማካበት ከመባዘን ይልቅ ለምን እንደምንኖር በተጋን ለማወቅ አዝ፦ ለምንድነው የምንኖረው እስትንፋሳችን የሚቀጥለው ዘመን ሲጨመር በእድሜያችን ላይ ለሰራን ጌታ እንድንሰራ አይደል ወይ (3x)