Song Lyrics

መለሰን

Meskerem Getu
Mengistih Timta
እንጀራ ልንበላ አልተከተልንህም ሃብት ብልጥግና ወደ አንተ አልጠራንም ለምድር በረከት ታይቶ ለሚጠፋ መች ደምህ ፈሰሰ ለሚያልፍ ተስፋ የዘላለም ሕይወት ማግኘታችን ጉዳይ ሁሌም ብርቃችን ነው ከምን ጋር ሊተያይ ሕይወት ያካፈልከን ኢየሱስ አንተ ነህ ሌላ አላየንም በነፍሱ የጨከነ ግን ዛሬ ሲመጣ በየአደባባዩ ትኩረት የሚፈልግ የሚል እኔን እዩ አንተን አደብዝዞ ራሱን የሚያጐላ አባብሎ ወሰደን ሆነናል ተላላ አዝ፦ አቤቱ ሕዝብህን መልሰን ሳንጠፋ ቀድመህ ድረስልን አቤቱ ልጆችህን አስበን ከድፍረት ከውድቀት ታደገን በጐ በሚመስል ሃሳብ እየተሳበ በመልካም ንግግር ሕዝብ ተሰበሰበ ዓመጸ ማይከለክል የረሳ ፍርድህን እራሳችንን እንዳናይ አደንዝዞ አሰረን በዘመን ፍጻሜ ጫፍ ላይ ሆነን ሳለን ልባችን እንዳያይ ምንው ተደለለ ዘይታችንን እንሙላ ጊዜው ሳይገባደድ ፈጥነን እንመለስ ከሄድንበት መንገድ አዝ፦ አቤቱ ሕዝብህን መልሰን ሳንጠፋ ቀድመህ ድረስልን አቤቱ ልጆችህን አስበን ከድፍረት ከውድቀት ታደገን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection