Song Lyrics

ለኔ ያለህ ትኩረት

Meskerem Getu
Mengistih Timta
ለኔያለህ ፍቅር ያስገርመኛል ለኔ ያለህ ምህረት ያስደንቀኛል ለኔ ያለህ ትዕግሥት ያስገርመኛል ለኔ ያለህ ትኩረት ያስደንቀኛል መተላለፌን ደምስሰህ ተቀበልከኝ በመንገዴ እንድጠፋ መቼ ተውከኝ ከፊቴ ሆነህ እግሮቼን የምትመራ ስጋቴን ሰብረህልኛል እንዳልፈራ በጎ ስጦታ ፍፁም በረከት ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል በምህረት በነፍስህ የገዛሃት ይቺ ነፍሴ ምሥጋናህን አትረሳም ሁልጊዜ አዝ፦ ለኔ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል ለኔ ያለህ ምህረት ያስደንቀኛል ለኔ ያለህ ትዕግሥት ያስገርመኛል ለኔ ያለህ ትኩረት ያስደንቀኛል የውስጤን ነገር ምነግርህ የማወጋህ ልቤ በአንተ ተማምኖ ተረጋጋ አሳረፍከኝ ወደ እኔ ተመልክተህ ጩኸቴን የሚሰማ ማን እንዳንተ በጎ ስጦታ ፍፁም በረከት ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል በምህረት በነፍስህ የገዛሃት ይቺ ነፍሴ ምሥጋናህን አትረሳም ሁልጊዜ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection