Song Lyrics

አንተ ተሰበክ

Meskerem Getu
Mengistih Timta
በእድሜ ጠዋት ልጅ ሳለው አግኝተህ ተንከባክበህ ያዝከኝ በሚያስገርም ትግስትህ እንዳገለግልህ እድሉን አገኘሁኝ ስላንተ እንድናገር በህዝብህ ፊት አቆምከኝ እኔ ልታከብረኝ ክብርህን ትተሀል (2x) ከሰማይ ሰማያት ስለኔ ወርደሀል (2x) የማልጠቅም ስሆን ሰው አድርገኸኛል ልጅህ አርገኸኛል በኔ ፈንታ ሞተህ (አስገኝተኸኛል) 2x ውድዬ አንተ ክበር ኧረ አንተ ንገሥ አንተ ነግሰህ ታይ በኔ ላይ አንተ ከብረህ ታይ ከመሬት አንስተህ በከፍታ ስፍራ እግሮቼ ሲቆሙ ጌትነትህ ይግነን ከፍ ከፍ ያድርጉህ ባንተ ይደመሙ ዛሬ ቀን ከወጣ በህዝብህ ፊት ብቆም በኔ ላይ ብትሰራ ሰዉ ሁሉ አንተን ይይ በሀገር በምድሩ ስላንተ ይወራ አንተ ተወራ ክብሬ ነህ አንተ ተወራ ድምቀቴ አንተ ተወራ ውበቴ አንተ ተወራ የኔጌታ አንተ ከብረህ ታይ በእኔ ላይ አንተ ገንነህ ታይ እኔን ልታከብረኝ ክብርህን ትተሀል ክብርህን ትተሀል ከሰማይ ሰማያት ስለኔ ወርደሀል በረት ተወልደሃል የማልጠቅም ሳለሁ ሰው አድርገኸኛል ልጅህ አርገኸኛል በኔ ፈንታ ሞተህ አስገኝተኸኛል [x2] ውድዬ አንተ ክበር ኧረ አንተ ክበር አንተ ድመቅ ኢየሱስ አንተ ድመቅ ጌታዬ አንተ ክበር ኧረ አንተ ድመቅ በበደሌ ምክንያት የተፈረደብኝ ነበርኩኝ የወደኩ ጌታዬ አነሳኸኝ ሀጥያቴ ተሽሮ በደምህ ታጠብኩኝ ባይገባኝ እንኳን ለኔ የሆንከው ነገር ፍቅርን ገልጦልኛል መርገሜን ወስደህልኝ ውዴ በኔ ፋንታ በአብ ፊት ታይተሀል አንተ ተወራ አረ እንተ ተሰበክ አንተ ከብረህ ታይ በኔ ላይ አንተ ነግሰህ ታይ አንተ ጎልተህ ታይ አንተ በርተህ ታይ አንተ ደምቀህ ታይ በኔ ላይ አንተ ጎልተህ ታይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection