Song Lyrics

ፍቅር ነህ

Meskerem Getu
Mengistih Timta
የዘላለም አምላክ የትውልድ መጠጊያ የፍጥረት መጋቢ ድጋፍ መሸሸጊያ ልጅህን በመስጠት ፍቅርን የተገበርክ ዓለሙን በሙሉ እንዲሁ የወደድክ ፍቅር ነህ እግዚአብሔር ይቅር ባይ የምትምር እልፍ ነው ቸርነትህ አይቆጠር (አይነገር )ማጽናናትህ(2x) ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ እያልኩ ባዜምልህ ደግሞ በአዲስ ምሕረት ታስደንቀኛለህ አምላኬ አምላኬ እልሃለው እጠራሃለው ደግሜ ልዩ ነው አወዳደድህ ላዚምልህ ፊትህ ቆሜ ምን ዓይነት ፍቅር ነህ እንዴት ያለህ መሃሪ(ወዳጅ) ነህ (2x) የዘላለም አምላክ የትውልድ መጠጊያ የፍጥረት መጋቢ ድጋፍ መሸሸጊያ ልጅህን በመስጠት ፍቅርን የተገበርክ ዓለሙን በሙሉ እንዲሁ የወደድክ ፍቅር ነህ እግዚአብሔር ይቅር ባይ የምትምር እልፍ ነው ቸርነትህ አይቆጠር (አይነገር )ማጽናናትህ(2x) የሕይወት ምንጭ ነህ ፍቅርን ለተጠማ የምታለመልም ነፍስን የምታረካ አውርቼ አውርቼ አልጠግብም አይገልጽህም ቃላቴ ደግነትህን ብዘምር አልገልጸውም በዚህ አንደበቴ ምን ዓይነት ፍቅር ነህ እንዴት ያለህ መሃሪ(ወዳጅ) ነህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection