Song Lyrics

ተሰሚ ነህ

Meskerem Getu
Mengistih Timta
ተሰሚ ነህ በሰማይ በምድር ጉልበት ሁሉ ሚንበረከክልህ የፈጠርከን እንሰግድልሃለን ሞገስህን ክብርህን እያየን ይሹሩን ሆይ በሰማያት ላይ ለእረድኤትህ በደመናት ላይ እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም ኧረ እንደርሱ ያለ ቢፈለግም የለም (2x) ዘመንህ ዘላለም ከቶ አታረጅም አምሳያ የለህም መቼም አትተካም አዬዬ መቼም አትተካም ፊትህ እንደ ፀሐይ በሀይል የሚያበራ ከዋክብት ጨረቃን ደመናን የሰራህ አዬዬ ፀሐይንየሰራህ የአማልክቱ አምላካቸው ነህ የፍጥረት ገዢ የዓለማት ንጉሥ ነህ ወሰን የሌለህ ስራህ እረቂቅ የማትታወቅ የሆንህ እጅግ ታላቅ እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም ኧረ እንዳንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም ኧረ እንዳንተ ያለ አይኖርም ዘላለም የዓለም ሁሉ መሪ ብርቱ ነህ ሀይለኛ ከሁሉ ቀዳሚ የሌለህ ፊተኛ አዬዬ የሌለህ ፊተኛ ይሁን ባልከው ቃልህ ሁሉ ተፈጠረ እቅድህ ግሩም ነው ስራህም ያማረ አዬዬ ስራህም ያማረ የአማልክቱ አምላካቸው ነህ የፍጥረት ገዢ የዓለማት ንጉሥ ነህ ወሰን የሌለህ ስራህ እረቂቅ የማትታወቅ የሆንህ እጅግ ታላቅ እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም ኧረ እንዳንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም ኧረ እንዳንተ ያለ አይኖርም ዘላለም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection