Song Lyrics

ለእኔ መሞቱን

Meskerem Getu
Eketelihalew
ተስፋ ሰጥቶኝ ሄደ የርስቴን መያዣ መንፈሱን ላከልኝ ለሕይወቴ ማደሻ የዘለዓለም ሕይወት ማግኛ መንገዱን አሳይቶኝ ሄዷል ለእኔ መሞቱን አዝ፦ ለእኔ መሞቱን ለእኔ መሞቱን (4x) በምድር እስካለሁ እስካሁን ድረስ ሳዝን የሚያበረታኝ እምባዬን ሚያብስ በርስቴ መያዣ በታረምኩበት ዘለዓለም እኖራለሁ በእርሱ መጽናናት አዝ፦ ለእኔ መሞቱን ለእኔ መሞቱን (4x) አሁን አውቄያለሁ የሚረባኝን በኑሮዬ ሁሉ ላይ መሾም ያለብኝን የእኔ መጀመሪያ ብሎም መጨረሺያዬ ከምንም ከማንም በላይ ኢየሱስ ነው ጌታዬ (2x) ዘላቂ ላልሆነው ለጊዜያዊው ደስታ እራሴን አላቀርብም ለሚያልቀው በዋይታ በመጠበቂያዬ ላይ እርሱን እጠብቃለሁ አይቀርም ይመጣል ጌታን አምነዋለሁ አዝ፦ ለእኔ መሞቱን ለእኔ መሞቱን (4x) አሁን አውቄያለሁ የሚረባኝን በኑሮዬ ሁሉ ላይ መሾም ያለብኝን የእኔ መጀመሪያ ብሎም መጨረሺያዬ ከምንም ከማንም በላይ ኢየሱስ ነው ጌታዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection