Song Lyrics

ጥበብን የሚሰጥ

Meskerem Getu
Eketelihalew
ጥበብን የሚሰጥ ጥበበኛ የሕይወት ውኃ ወንዝ የእኔ መገኛ እግዚአብሔር እርሱ የእኔ ነው ኧረ/እስቲ ማነው ከእኔ ሚለየው (2x) ልጅ ቢወለድ ከባለጠጋ ይካፈላል ከአባቱ ጋር ሃብቱ ሁሉም ቅርሱ የእርሱ ነው ግን የሚያልፍ ጊዜያዊ ነው የእኔስ አባት ከሁሉ የላቀ ሁሉን ገዢ በዓለም የታወቀ እኮራለሁ ልጁ በመሆኔ ኤልሻዳይ ነው አባቴ ለእኔ ኃጢአት አልስራ እንጂ የማያከብረውን ሌላ ምን ይኖራል እኔና እርሱን ሚለየን በፀጋው በርትቼ እኖርለታለሁ እንደ ሚያግዘኝ ጌታን አምነዋለሁ አባ አባ ብዬ ስለው አቤት ሚለኝ የቅርቤ ነው ሚጠብቀኝ እንደ ዓይኑ ብሌን ማን ሊወስደው ከእኔ ጌታዬን የእኔስ አባት ከሁሉ የላቀ ሁሉን ገዢ በዓለም የታወቀ እኮራለሁ ልጁ በመሆኔ ኤልሻዳይ ነው አባቴ ለእኔ ኃጢአት አልስራ እንጂ የማያከብረውን ሌላ ምን ይኖራል እኔና እርሱን ሚለየን በፀጋው በርትቼ እኖርለታለሁ እንደ ሚያግዘኝ ጌታን አምነዋለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection