Song Lyrics

አማኑኤል

Meskerem Getu
Eketelihalew
በለጋነት ልቤ ፍቅርህ አሸንፎኛል ከአንተ የትም አልሄድም አንተ ተመችተኸኛል ቃላትም የማይገልጹት ሰማያዊ ደስታ በህይወት መመስከር መገዛት ለጌታ እኔ ለብቻዬ ስሆን ጌታን አውቀዋለሁ የአባትነቱን ፍቅር ቀምሻለሁ ጌታን አውቀዋለሁ ጌታን አመልካለሁ ለጌታ እገዛለሁ ጌታን እወደዋለሁ ኢየሱሴ አንተን ምን ብዬ ልግለጽህ ቃላቶች አነሱ በምን ልተርክህ እስከ ዛሬ ማውቀው የሚደንቅ ነገር እጅጉን ትንሽ ነው ከአንተ ሲወዳደር አማኑኤል (አማኑኤል) ፤ አማኑኤል አማኑኤል (ከእኔ ጋር ነው) ከእኔ ጋር ነው እግዚአብሔር (እግዚአብሔር) አባት ለልጆቹ ሃይማኖት ያወርሳል ልጅ የተማረውን ስርዓት ይፈጽማል ግን የጌታን ፍቅር አላስተዋለውም ሃይማኖቱን እንጂ ጌታን ከቶ አልተቀበለም ጌታዬ ግን ድኅነት ለሚሹህ ቅርብ ነህ አንተ ትሻሃላለህ አንተ ታዋጣለህ አምላኬ ሆይ አንተን ተረድቼሃለሁ በወረስኩት ሳይሆን በግሌ አውቅሃለሁ ከቤትህ ርቄ ወዴት እሄዳለሁ ፍቅርህ ማርኮኛል አንተን መርጫለሁ አማኑኤል (አማኑኤል) ፤ አማኑኤል አማኑኤል (ከእኔ ጋር ነው) ከእኔ ጋር ነው እግዚአብሔር (እግዚአብሔር)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection