Song Lyrics

ላይተወኝ ቃል ገብቶአል

Meskerem Getu
Eketelihalew
ያላዩት አገር አይናፍቅም እንደሚሉት ሰዎች ተረት አይደለም ዓይኔ አይቶት ነው የልቦናዬ ሕይወቴን እንካ ኑሮዬን እንካ ብዬ የሰጠሁት ለዚህ ጌታዬ ዛሬም ፍቅሩ ያዘኝ ምህረቱ ያዘኝ ፀጋው ያዘኝ ያዘኝ (5x) ያዘኝ (4x) ላይተወኝ ቃል ገብቷል ላይጥለኝ የጌታዬ ፍቅሩ ማረከኝ (2x) ሰላሙን ሞላ በቤቴ ተለወጠልኝ ሕይወቴ በቀኙ ደግፎ ያዘኝ መንፈሱ አሳረፈኝ አሁን አሁንማ (አሁንማ) ለሌላው አተረፈኝ ኢየሱስ ደረሰልኝ (2x) ልዑል መጠጊያ ሆነኝ በክንፉ አሳረፈኝ ልቤ ከሥጋት አረፈ ጽዋዬ እየተረፈ (2x) አሁን አሁንማ (አሁንማ) ለሌላው አተረፈኝ ኢየሱስ ደረሰልኝ (2x) በጠላቶቼ ፊት ለፊት ቀባኝ አምላኬ በዘይት ገመዴ ባማረ ስፍራ ወደቀች/ወድቃለች ልቤ እንዳይፈራ (2x) አሁን አሁንማ (አሁንማ) ለሌላው አተረፈኝ ኢየሱስ ደረሰልኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection