Song Lyrics

አይዞህ

Meskerem Getu
Eketelihalew
ነገን ነገን ስታይ ቢጨልምብህ/ከጨልምብህ በተስፋ ተራመድ እራዕይ ይኑርህ/አለህ (2x) አይዞህ (3x) ሥራ ብታጣ ገንዘብ ቢጠፋ ቢጨልምብህ አይዞህ ሚረዳህ አጥተህ ብቻህን ብትሆን ተስፋ ባይኖርህ አይዞህ (2x) አስሩን ስታስብ ሚሰማህ እንዳነስህ ከሁሉ የበታች የሆንክ የመሰለህ አይዞህ (3x) ልዩ የሆነ ችሎታ አለህ ተነስ ታገል አይዞህ ከማንም አታንስ ይኸው ራስህም ብቃት እኮ አለህ አይዞህ መስራት ማችልበት ምንም ምክኒያት የለ ጠንክረህ ብትሰራ ብዙ ታጭዳለህ አይዞህ (3x) የረፈደብህ እየመሰልህ ትተክዛለህ አይዞህ በዚህ ጉብዝናህ በሙሉ ኃይልህ መራመድ ጀምር አይዞህ አንድ ቀን ያልፋል (3x) የወደደ ያከበረ ያፈቀረ አምላክ አለህ አለህ የወደደ ያፈቀረ ያከበረ አምላክ አለህ አለህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection