ለኔ ከላይ ከሰማይ (2x) መሞት የሚገባኝ ነበርኩ መጣልኝ ሲሳይ አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው ለእኔ እንደዚህ የሚያደርገው ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (2x) ከላይ ከሰማይ የባሪያን መልክ ይዞ በእኔ በኃጢአተኛዋ በፍቅር ተይዞ ካለሁበት አዘቅት ከሞት ሊያወጣኝ እርሱ ዋጋ ከፍሎ ነጻ ነሽ አለኝ አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው ለእኔ እንደዚህ የሚያደርገው ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (2x) በዚያ በጐልጐታ በቀራኒዮ ላይ ከቶ መች አፈረ እርቃኑ ሲታይ የህማም ሰው ሆነ ተመታ በደዌ እርሱ ዋጋ ከፍሎ ይኸው ዳንኩኝ አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው ለእኔ እንደዚህ የሚያደርገው ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (2x) ወርዱና ስፋቱ የማይለካው ጥልቅ ነው ፍቅሩ ወሰን የሌለው የልቤ አይወጣም ብዙ ቃል ደርድሬ ሳመሰግን ብውል በመልካም ዝማሬ ለእኔ ከላይ ከሰማይ (2x) መሞት የሚገባኝ ነበርኩ መጣልኝ ሲሳይ አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው ለእኔ እንደዚህ የሚያደርገው ከእኔ ምንም/አንዳች የለ (2x)